የኢትዮ ጀርመን የስፕርትና ባህል የ2 ቀን ዝግጅት ታሪካዊ አመጣጥ

ከ10 ዓመት በላይ ዝግጅቱ በአንድ ቀን ብቻ ይጠናቀቅ ነበር። ነገር ገን የቀኑ ማጠር ለብዙሃኑ ስላልተመቸ አሳቻና ሁነኛ ቀን በመፈለግ ዝግጅቱ ከአንድ ቀን ወደ 2 ቀን ተቀይሮዋል። ይህም እቅድ እንዲሳካ ከቅዳሜና እሁድ ጋር ተለጥፎ በ3ኛ የእረፍት ቀንነቱ የሚታወቀውን ፊንግስተንን እንደ አማራጭ ተወስዶዋል። የፊንግስተን ሰኞ ወገኖች ተረጋግተው ወደ የመጡበት ለመመለስ ይችላሉ በሚል ህሳቤ ነው።
ይህም እቅድ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2017 በበርሊ ከተማ በኢትዮ በርሊን አዘጋጅነት እውን ሆኖዋል። በመቀጠል 2018 በፍራንፈርት ተዘጋጅቶ ምርጥነቱ በድጋሚ ተረጋግጦዋል።
የ2019ኙ አዘጋጅ ኢትዮዳርምሽታትም በዚሁ ቀን ለማዘጋጀት ቃል ገብቶ እድሉ ተሰጥቶት ዝግጅቱን ወስዶዋል። ነገር ግን በመጨረሻው ሰዓት ከነሱ ዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት የተፈቀደው ሜዳ ላይ ሌላ ተለጣፊ ዝግጅት ባለመዳዎቹ ስላዘጋጁ ይህም ደግሞ የዝግጅቱን ገፅታና የእግር ኻስ ጨማታውን የሚያውክ ሆኖ ስለተገኘ በዚህ ዓመት ሳይሳካ ቀርቶዋል።
ይህም ሆኖ በሚገርምና በሚደንቅ ሁኔታ ሁሉም ቡድኖች ከኢትዮ ዳርምሽታት ጎን በመቆም ዝግጅቱ በተሳካና በጥሩ ሁኔታ እንዲያልፍ ረድተዋል።
በመጨረሻም ለመደፊቱ ይህ ነገር እንዳይደገም የመፍትሄ ሃሳቦችን በማሰባሰብ በሚቀጥለው የኢትዮ ጀርመን ውድድር ላዩ የኢትዮ ሃምቡርግ ቡድን ጋር በመሆን በርሊን የተጠነሰሰውንና ፍራንክፈርት ላይ ያጣጣምነውን የፊንግስተን የእረፍት ቀኖች ለጥሩ ስብስብና ለንፁህ ኢቶጵያዊነት በድጋሚ ሃምቡርግ ላይ እንደምንደግመው ጥርጥር የለውም።
ስፖርት ለጤንነት ለምርት ለወዳጅነት
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Follow by Email
YouTube
Instagram